ታላቅ የምሥራች ለአርባ ምንጭ ከተማ!!
እግዚአብሔር ረድቶን በብዙ ከተሞች ላይ ገብተን የማይቆጠሩ ተዓምራቶችን እግዚአብሔር ለብዙዎች አድርጎ እስከዛሬ ድረስ እየተናገሩና እየመሠከሩ ይገኛሉ።
አሁን ደግሞ በበርካቶቻችሁ ጥያቄ መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ ላይ የካቲት 18, 19, 20, አርብ፣ ቅዳሜና፣ እሑድ፤ ታላቅ የወንጌል ክሩሴድ በአርባ ምንጭ ቡቡ ሜዳ ላይ ተዘጋጅቷል።
በእነዚህ ተከታታይ ቀናት በጣም የምንወደውና የምናከብረው በወንጌልና በእግዚአብሔር ጸጋ በምድራችን ላይ የተነሣው ነብይ ዘካርያስ ወንድሙ ያገለግለናል።
የእግዚአብሔር ክንድ በከተማዋ ላይ አነጋጋሪ ነገሮችን ያደርጋል።
በተለያዩ ከተሞች ላይ ሲገለጥ የነበረው የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን እጅ በአርባ ምንጭ ከተማ ላይም በሚያስደንቅ ሁኔታ ሢሰራ በግልጽ እናያለን።
በየትኛውም በሰው ጥበብ መፍትሔ ያጡ ነገሮች ሁሉ በእነዚህ ቀናት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ምላሽ ያገኛሉ።
ማንኛውም አጋንንታዊና መናፍስታዊ እስራቶች ይበጠሳሉ።
ይሄ ቀን ለብዙዎች የአርነት፣ የመፈታት፣ የፈውስና የተዓምራት ቀን ይሆናል።
ቀኑን በፍጹም እንዳትረሱ የካቲት 18, 19, 20, አርብ፣ ቅዳሜ፣ እሑድ፤ ክሩሴዱ ይካሄዳል።
“የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል።”
— ኢዮብ 9፥10