በምድራችን ላይ እግዚአብሔር ቀብቶ ካስነሣው ከእግዚአብሔር ሰው ነብይ ዘካርያስ ወንድሙ ጋር በርካታ ዘማሪዎች የታደሙበት አነጋጋሪው ክሩሴድ በሚታይና በሚዳሰስ ድንቅና ተዓምራት ተትረፍ::
እንዲህ ዓይነት የእግዚአብሔር የማዳን ጣት የተገለጠበት የድንቅና የተዓምራት ክሩሴድ በወንጌል ኃይል ካልሆነ በስተቀር በምንም የሰው ልጅ ጥበብ የማይደገም ሆኖ አልፏል።
ከዊልቸር የተነሡ ወገኖችን በመካከላችን አይተናል፤ በሜዳው የነበረው ሕዝብ ሁሉ ይሄንን ለዓይን የማይታመን ተዓምራት ሲመለከት ሊቋረጥ በማይችል የአምልኮ መንፈስ ተሞልቶ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በታላቅ መደነቅ አምልኳል።
በርካቶች ክራንቻቸው ጥለው እየዘለሉና እየሮጡ እውነትም ኢየሱስ ጌታ ነው ብለው አውጀዋል። ከልዩ ልዩ በሽታዎች የተፈወሱ ሰዎች ቁጥርም ከልክ በላይ ከመሆኑ የተነሣ ለምክርነት የሚሆን ጊዜ እስኪያጥር ድረስ ደርሶ ብዙዎች ፈውሳቸውን ተቀብለው በእልልታ ተመልሰዋል።
ብዙዎች እንዲህ ዓይነት ነገር አይተን አናውቅም አስኪሉ ድረስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በከተማው አስደናቂ ድንቅና ተዓምራቶችን ሠርቷል።
ይሄንን ድንቅና ተዓምራት የተመለከቱ በቁጥር በርካታ ሰዎች ክርስቶስ ኢየሱስን የሕይወታቸው ጌታ አድርገው ተቀብለዋል።
“እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ በምልክትና በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ ተአምራትም፥ መንፈስ ቅዱስንም በማደል አብሮ መሰከረለት።”
— ዕብራውያን 2፥4
ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻውን ያድናል!!
MORE!!!……