የገጠር የወንጌል አገልግሎት

We are a church that believes in Jesus Christ and the followers and This is where you should start.

ይህ አገልግሎት ከተጀመረ የቆየ ሲሆን ብዙዎችን በገበያና በእርሻ ቦታቸው እንዲሁም በቤታቸው ሳይቀር በግልና በጀማ ወንጌልን የሚሰሙበት አጋጣሚ የፈጠረ ተልዕኮ እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም የወንጌል አንቅስቃሴ ብዙዎች ክርስቶስ ኢየሱስን ከመተዋወቃቸውም በላይ በርካታዎች በስሙ ተጠምቀዋል፤ ቤተክርስቲያን በሌለባቸው ቦታዎች ላይ ቤተክርስቲያንን በመትከል ሕዘቡ ከባዕድ አምልኮ የሚላቀቅበትን መንገድ በወንጌል ኃይል ማደረግ ችለናል።
የሚገርመው ይሄ አገልግሎት የተጀመረው ከኮሮና በፊት ሲሆን covid 19 ተስፋፈቶ ቤተክርስቲያን በተዘጋችበት ወቅት እንኳን እንቅስቃሴው ይበልጥ ቀጥሎ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ክርስቶስን ተቀብለው በርካቶችም ስለ አዳኝነቱ ሰምተዋል።
አሁን ባለነበት በዚህ ጊዜ እንኳን በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመዘዋወር ወንጌልን በገበያ በጎዳናዎች ላይ እንዲሁም ቤት ለቤት እየገባን እየሠራን እንገኛለን።
እነዚህ የምትመለከቷቸው እኅትና ወንድሞቻችን በዚህ ዓይነት መንገድ ወንጌል የደረሳቸው እና በአካባቢያቸው አጥቢያ ቤተክርስቲያን ተተክሎ ወደ ክርስቶስ የፈለሱ ናቸዉ። ከዚህ ቀደም የነበረን አዳራሽ በህዝብ ቁጥር ብዛት ስለተጨናነቀ አዲስ እያሰራን ወዳለንው አዳራሽ ገብተናል። ለዚህም ልኡል አምላክ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን።
ወንጌል ኢየሱስ ነው!!!!!!

Post navigation