በአርባ ምንጭ ምድር ላይ በወንጌል ታሪክ ተሠራ።
በአርባ ምንጭ ምድር በአደባባይ የወንጌል ስርጭት ተካሄደ።
ይህ የወንጌል ሥርጭት ታሪካዊ ከመሆኑም በላይ የኢየሱስ አዳኝነት በይፋና በግልጽ የተሰበከት በርካቶች የክርስቶስን አዳኝነት የሰሙበት ታላቅ የጀማ እንቅስቃሴ የታየበት ነበር።
ከዚህ የተነሣ በከተማው ያሉ አማኞችም የዚህ አይነቱን እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ያነሣሣና በተለይም በከተማው አብዛኛው ሰው ወንጌልን ካለመቀበሉ ጋር ተያይዞ የዚህ አይነቱ ንቅናቄ በየጊዜው እንዲደረግ መንገድ ያመላከተና አቅጣጫ ያሳየ ነበር ማለት ይቻላል።
በዚህም የከተማው አማኞች ደስታቸውን የገለጹበት መሆኑን ተመልክተናል።
እጅግ ደስ ያለን ደግሞ በጣም ብዙ ሰዎች ያለምንም ማመንታት በጎዳናው ላይ ተንበርክከው ንስሐ በመግባት ክርስቶስ ኢየሱስን የግል አዳኛቸው አድርገው ተቀብለዋል። ከአጋንንት እስራትም የተፈቱ ነበሩ።
ኢየሱስ ጌታ ነው!!